የፊደል ገበታ ላይ ያሉትን ፊደሎች በሙሉ መተየብ ያስተምራል። 133 ትምህርቶች በአምስት ደረጃዎች ተከፍለው፣ በፍጥነትና በትክክለኛነት እየተመዘኑ ይቀጥላሉ።
FidelTyping teaches you to type every letter on the fidel chart: free online typing practice for Ethiopian languages, in 133 lessons across five stages, each one scored on speed and accuracy.
Fidel chart·Letter recognition·Timed test·Your own text·Placement·How it works
FidelTyping ለኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተብሎ የተሰራ ነጻ ትየባ ማለማመጃ ነው። አብዛኞቹ የአማርኛ ትየባ ማስተማሪያዎች ያልተሟሉ እንዲሁም ደረጃ በደረጃ የሚያሰለጥኑ አይደሉም። ይህ ግን ከጀማሪ እስከ ሊቅ ደረጃ ማለትም በፍጥነትና በቅልጥፍና መተየብ የሚችሉበት ደረጃ እስከሚደርሱ ድረስ ደረጃ በደረጃ ያሰለጥናል።
FidelTyping is a free typing trainer built for Ethiopian languages. Most Amharic typing tools are incomplete, and they do not train you stage by stage. This one does: from beginner to expert, one stage at a time, until you reach the point where you type with real speed and fluency.
ዘጠኙም ቋንቋዎች ተመሳሳይ መሰልጠኛ ይዘት ተዘጋጅቶላቸዋል፦ አማርኛ፣ ትግሪኛ፣ ግዕዝ፣ አዊኛ፣ ሰባትቤት፣ ስልጤኛ፣ ሀደሪኛ፣ ቤንችኛ እና ሙርሲኛ። እያንዳንዱ ከራሱ ፊደል የተገነባ ሥርዓተ ትምህርት አለው፤ ስለዚህ የትግሪኛ ወይም የሌላ ቋንቋ ተማሪ ቋንቋው የማይጠቀምባቸውን ፊደላት አይለማመድም። የቃላት ክምችትና የቅልጥፍና ደረጃ ለጊዜው በአማርኛ ብቻ ነው።
All nine languages have the same training content prepared for them: Amharic, Tigrinya, Ge’ez, Awi, Sebatbeit, Silt’e, Harari, Bench and Mursi. Each has a curriculum built from its own alphabet, so a Tigrinya learner — or a learner of any other language — never practises letters their language does not use. Word pools and the fluency stage are Amharic-only for now.
በኢትዮጵያ ቋንቋዎች በፍጥነትና በቅልጥፍና መተየብ ለሚፈልግ ከልጅ እስከ አዋቂ በየትኛውም የዓለም ክፍል ለሚኖሩ ሁሉ ይሆናል። ክፍያ የለውም፤ መጫን አያስፈልግም፤ አካውንትም አይጠየቅም። በኮምፒውተር ቁልፍ ሰሌዳ ወይም በስልክ ማያ ገጽ ላይ በአሳሹ ውስጥ ይለማመዱ። በተለማመዱ ቁጥር የትየባ ክህሎትዎ ለውጥ አካውንት ሳይኖርዎት እንኳ ይቀመጣል።
For anyone who wants to type the Ethiopian languages with speed and fluency — child or adult, anywhere in the world. There is no charge, no installation and no account required. Practise in the browser, on a computer keyboard or on the screen of a phone. Every time you practise, the change in your typing skill is saved, even without an account.