ወደ ዋናው ይዘት ይዝለሉ · Skip to main content
ፊደልTyping
  • እድገትProgress
ይግቡLoginይግቡ · Login

የመነሻ ረድፍ · ጠቋሚና መሐል ጣቶች · ሳድስ

Home row · index and middle fingers · sadis

—
ፍጥነት · WPM
—
ትክክለኛነት · ACC
የደመቀውን ፊደል ይተይቡ።Type the highlighted fidel.ለመጻፍ ከታች ያሉትን ቁልፎች ይንኩ · Tap the keys below to type
ፊደል ማንበብ አይችሉም? በመጀመሪያ ማንበብ ይማሩ · Cannot read fidel yet? Start with the letters
ፍፍፍፍ ጅጅጅጅ ድድድድ ክክክክ
ፍ ይተይቡ · Type ፍ

ፊደላቱን ይተዋወቁ · Meet the letters

በፊደል መተየብ ይማሩ · Learn to type Ethiopic

የፊደል ገበታ ላይ ያሉትን ፊደሎች በሙሉ መተየብ ያስተምራል። 133 ትምህርቶች በአምስት ደረጃዎች ተከፍለው፣ በፍጥነትና በትክክለኛነት እየተመዘኑ ይቀጥላሉ።

FidelTyping teaches you to type every letter on the fidel chart: free online typing practice for Ethiopian languages, in 133 lessons across five stages, each one scored on speed and accuracy.

ፊደል ገበታ · Fidel chartፊደል ማንበብ · Letter recognitionየፍጥነት ምዘና · Timed testየራስዎ ጽሑፍ · Your own textምደባ · Placementእንዴት ይሠራል · How it works

▸ስለዚህ ስልጠና · About this course

ስልጠናው ምን ያስተምራል · What the course teaches

FidelTyping ለኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተብሎ የተሰራ ነጻ ትየባ ማለማመጃ ነው። አብዛኞቹ የአማርኛ ትየባ ማስተማሪያዎች ያልተሟሉ እንዲሁም ደረጃ በደረጃ የሚያሰለጥኑ አይደሉም። ይህ ግን ከጀማሪ እስከ ሊቅ ደረጃ ማለትም በፍጥነትና በቅልጥፍና መተየብ የሚችሉበት ደረጃ እስከሚደርሱ ድረስ ደረጃ በደረጃ ያሰለጥናል።

FidelTyping is a free typing trainer built for Ethiopian languages. Most Amharic typing tools are incomplete, and they do not train you stage by stage. This one does: from beginner to expert, one stage at a time, until you reach the point where you type with real speed and fluency.

አምስቱ ደረጃዎች · The five stages

  • 1. ሳድስ ብቻ · Sadis onlyአንድ ፊደል ለአንድ ቁልፍ ጥምረት።One fidel to one key combination.
  • 2. ሳድስ ያልሆኑ · Everything but sadisየተቀሩትን ሳድስ ያልሆኑ የሁሉንም ፊደል ተራ ሆሄያት ያለማምዳል።Drills the remaining non-sadis orders of every basic fidel.
  • 3. ሞክሼና ተጨማሪ ፊደላት · Look-alike and additional lettersሐ ኀ ሠ ጸ ፀ ዐ ከሞክሼአቸው የሚለዩት በቁልፍ ብቻ ነው።ሐ ኀ ሠ ጸ ፀ ዐ — separated from their look-alikes by the keystroke alone.
  • 4. ዲቃላ ፊደላትና ቁጥሮች · Diqala letters and numeralsየራብዕ-ዲቃላና ዲቃላ ፊደላት፣ እንዲሁም የግዕዝ ቁጥሮች።The long tail — rounded forms, the five-order families, and Ge’ez numerals.
  • 5. ቅልጥፍና · Fluencyበእውነተኛ ጽሑፍ ላይ ፍጥነትና ቅልጥፍና ያስለምዳል።Builds speed and fluency on real text.

ቋንቋዎች · The languages

ዘጠኙም ቋንቋዎች ተመሳሳይ መሰልጠኛ ይዘት ተዘጋጅቶላቸዋል፦ አማርኛ፣ ትግሪኛ፣ ግዕዝ፣ አዊኛ፣ ሰባትቤት፣ ስልጤኛ፣ ሀደሪኛ፣ ቤንችኛ እና ሙርሲኛ። እያንዳንዱ ከራሱ ፊደል የተገነባ ሥርዓተ ትምህርት አለው፤ ስለዚህ የትግሪኛ ወይም የሌላ ቋንቋ ተማሪ ቋንቋው የማይጠቀምባቸውን ፊደላት አይለማመድም። የቃላት ክምችትና የቅልጥፍና ደረጃ ለጊዜው በአማርኛ ብቻ ነው።

All nine languages have the same training content prepared for them: Amharic, Tigrinya, Ge’ez, Awi, Sebatbeit, Silt’e, Harari, Bench and Mursi. Each has a curriculum built from its own alphabet, so a Tigrinya learner — or a learner of any other language — never practises letters their language does not use. Word pools and the fluency stage are Amharic-only for now.

የፊደል ገበታዎቹ · Their alphabets: አማርኛ · Amharic,ትግሪኛ · Tigrinya,ግዕዝ · Ge'ez,አዊኛ · Awi,ሰባትቤት · Sebatbeit,ስልጤኛ · Silt'e,ሀደሪኛ · Harari,ቤንችኛ · Bench,ሙርሲኛ · Mursi

ለማን ነው · Who it is for

በኢትዮጵያ ቋንቋዎች በፍጥነትና በቅልጥፍና መተየብ ለሚፈልግ ከልጅ እስከ አዋቂ በየትኛውም የዓለም ክፍል ለሚኖሩ ሁሉ ይሆናል። ክፍያ የለውም፤ መጫን አያስፈልግም፤ አካውንትም አይጠየቅም። በኮምፒውተር ቁልፍ ሰሌዳ ወይም በስልክ ማያ ገጽ ላይ በአሳሹ ውስጥ ይለማመዱ። በተለማመዱ ቁጥር የትየባ ክህሎትዎ ለውጥ አካውንት ሳይኖርዎት እንኳ ይቀመጣል።

For anyone who wants to type the Ethiopian languages with speed and fluency — child or adult, anywhere in the world. There is no charge, no installation and no account required. Practise in the browser, on a computer keyboard or on the screen of a phone. Every time you practise, the change in your typing skill is saved, even without an account.

ፊደልTypingለኢትዮጵያ ቋንቋዎች የትየባ ማለማመጃ · Ethiopian typing trainer
ስለ እኛ · Aboutየግላዊነት ፖሊሲ · Privacy Policy
© 2026 A. Wondosen · መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው · All rights reserved